BBC News, አማርኛ - ዜና
BBC News Amharic Top Stories
ኢትዮጵያ ውስጥ ሴቶች ከወንዶች እና ሌሎች ማንነቶች በበለጠ በማኅበራዊ ሚዲያ የጥላቻ ንግግር ያስተናግዳሉ - ጥናት
ኢትዮጵያ ውስጥ በፌስቡክ፣ ቴሌግራም እና ትዊተር ላይ ሴቶች ከወንዶች እንዲሁም ከብሔር እና የሀይማኖት ማንነቶች በበለጠ የጥላቻ ንግግር ሰለባ እንደሚሆኑ መቀመጫውን ዩናይትድ ኪንግደም ያደረገው ሴንተር ፎር ኢንፎርሜሽን ሪዚሊየንስ የተባለው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋም ያደረገው ጥናት አመለከተ።
“ኦሮሞ ነጻ ወጥቷል፤ ትናንትና ታግለን በደማችን አሸንፈናል”- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ በወለጋ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ዛሬ ማለዳ ሚያዝያ 30/2016 ዓ.ም የምስራቅ ወለጋ ዞን ከተማ ወደ ሆነችው ነቀምት አምርተው ባደረጉት ንግግር “ኦሮሞ ነጻ ወጥቷል፤ ትናንትና ታግለን በደማችን አሸንፈናል” ሲሉ ተናገሩ።
ለቦይንግ የሚቀርቡ የአውሮፕላን አካላት 'ከባድ ግድፈቶች' ነበሩባቸው ተባለ
በቦይንግ ትልቁ አቅራቢ የተዘጋጁ ፊውዝላጆች (አውሮፕላን ሰዎችን እና እቃዎችን የሚጭንበት ክፍል) ከባድ ግድፈቶች አዘውትረው እንደሚገኙባቸው የኩባንያው የቀድሞ የጥራት ተቆጣጣሪ ገለጹ።
የተሻለ ደመወዝ ፍለጋ እርሻ ጥለው የወጡ ማላውያንን እስራኤል አባረረች
የተሻለ ደመወዝ ፍለጋ እርሻ ጥለው የወጡ ማላውያንን እስረኤል አባረረች።
ግማሹ የጋዛ የውሃ ጣቢያ መጎዳቱን አሊያም መውደሙን የቢቢሲ ሳተላይት መረጃ አረጋገጠ
እስራኤል በሐማስ ላይ ወታደራዊ እርምጃ ከጀመረች ወዲህ በመቶዎች የሚቆጠሩ የጋዛ የውሃ እና የንፅህና መጠበቂያ ተቋማት ተጎድተዋል ወይም ወድመዋል ሲል የቢቢሲ የሳተላይት መረጃ አረጋግጧል።
እስራኤል ራፋህን ከወረረች አሜሪካ የተወሰነ መሣሪያ መላክ እንደምታቆም ባይደን አስጠቀቁ
እስራኤል በራፋህ ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት ከከፈተች አሜሪካ ከምትሰጣት የጦር መሣሪያ የተወሰነውን መላክ እንደምታቆም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስጠነቀቁ።
አስጊው የወንድ ብልት ካንሰር
የወንድ ብልት ካንሰር እምብዛም የሚከሰት ባይሆንም በሕመሙ ምክንያት የሚከሰት ሞት ቁጥር በመላው ዓለም እየተበራከተ ይገኛል።
የጋዛ ዋነኛ የሰብአዊ እርዳታ ማሳለፊያ የሆነችው ራፋህ
የተባበሩት መንግስታት እና ምዕራባውያን አስከፊ ሰብአዊ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል ቢያስጠነቅቁም እስራኤል ግን ለወራት በደቡባዊ ጋዛዋ ራፋህ ዘመቻ ልታደርግ መሆኑን ስትዝት ቆይታለች።
የኢትዮጵያ መንግሥት መጠለያ ጣቢያዎችን ለቀው የወጡ የሱዳን ስደተኞች ጉዳይ እንዳሳሰበው ገለጸ
የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት በአማራ ክልል በሚገኙት ኩመር እና አውላላ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች የደረሰው “አሳዛኝ ሁኔታ አስግቶኛል” አለ።
በኢትዮጵያ በጎርፍ አደጋ አንድ ሚሊዮን የሚሆኑ ሠዎች ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ገለጸ
የኢትዮጵያ ሚትዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት የ2016 ዓ.ም. የበልግ ወቅት በተለይም ዋነኛና ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑ አካባቢዎች ከመደበኛ በላይ የሆነ የዝናብ መጠንና ስርጭት እንደሚኖራቸው ትንበያ አውጥቷል። ባለፉት ሳምንታት ዋና ከተማዋን አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በደረሱ የጎርፍ አደጋዎች የሠው ሕይወት እልፈትና ለንብረት ጉዳት ደርሷል። በአዲስ አበባ በደረሰው አደጋ አራት ሰዎች በጎርፍ ተወስደው ህይወታቸውን ማለፉን የአዲስ አበባ ከተማ የእሳት እና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ለቢቢሲ አረጋግጧል።
በጥቃቶች ምክንያት ከአማራ ክልል የተመድ መጠለያ ጣቢያዎች ለቀው የወጡ የሱዳን ስደተኞች እርዳታ እንዲደረግላቸው ተማጸኑ
በደረሱባቸው ተደጋጋሚ ጥቃቶች ምክንያት በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ከሚገኙ ሁለት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መጠለያ ጣቢያዎች ለቀው የወጡ ሱዳናውያን ስደተኞች እርዳታ እና ጥበቃ እንዲደረግላቸው ተማጸኑ።
የሴት ልጅ ግርዛትን የተመለከተው አወዛጋቢው የኢትዮጵያ ዑለማዎች ውሳኔ
የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከጥቂት ሳምንታት በፊት ባወጣው መግለጫ ላይ የሴት ልጅ ግርዛትን በተመለከተ በቁጥር 12 እና 13 ላይ የሰፈረው ውሳኔ ከሴቶች መብት እንዲሁም ከኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንጻር ተቃርኖ እንዳለው እንደ “አዲስ ፓወር ሃውስ’’ እና “አርቲክል 35” ያሉ በሴቶች መብት ላይ የሚሠሩ ንቅናቄዎች በማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻቸው ድምጻቸውን እያስተጋቡ ነው።
አነጋጋሪ ጉዳይ
ጦርነቱን ተከትሎ በአማራ ክልል ስር የተቋቋሙ አስተዳደሮች እስከ ሰኔ 30 መፍትሔ እንደሚያገኙ ጄነራል ታደሰ ተናገሩ
የትግራይን ጦርነት ተከትሎ በአማራ ክልል ስር ተጠቅለው የተቋቋሙ አስተዳደራዊ መዋቅሮች እስከ ሰኔ 30/ 2016 ዓ.ም መፍትሔ እንደሚያገኙ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት ጄነራል ታደሰ ወረደ ተናገሩ።
የአውሮፓ ህብረት የጣለውን ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ ውሳኔ እንዲያጤነው ኢትዮጵያ ጠየቀች
የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ መንግሥት በህገወጥ መንገድ በአውሮፓ የሚኖሩ ዜጎቹን ለመቀበል ያሳየው ተባባሪነት አናሳ ነው በሚል በኢትዮጵያውያን ላይ የጣለው ጊዜያዊ የቪዛ ገደብ እንዳሳዘናት ኢትዮጵያ አስታወቀች።
ኢትዮጵያውያን ጉምቱ የሕክምና ባለሙያዎች ወደ ሩዋንዳ የሚፈልሱት ለምንድነው?
የካበተ ልምድ ያላቸው ኢትዮጵያውያን የሕክምና ባለሙያዎች በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ተፈላጊ ናቸው። ከእነዚህም መካከል የምሥራቅ አፍሪካዋ ትንሽዬ አገር ሩዋንዳ ኢትዮጵያውያኑን በመሳብ አንዷ ለመሆን ችላለች። በአገሪቱ ከመንግሥት ተቋማት ጀምሮ በትላልቅ ሆስፒታሎች ውስጥ ጥቂት የማይባሉ አንቱ የተባሉ ኢትዮጵያውያን ሐኪሞች በኃላፊነት ጭምር እየሠሩ ይገኛሉ። ታዲያ ኢትዮጵያውያኑን ሙያተኞች ወደ ሩዋንዳ የሚስባቸው ምን ይሆን?
አላማጣ እና ኮረም ከተሞች እንዴት እየሰነበቱ ነው?
የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነትን ተከትሎ በአማራ ክልል ስር ሲተዳደሩ የቆዩት የራያ አካባቢዎች ያለ አስተዳዳሪ ወደ ሁለተኛ ሳምንታቸው እየተሻገሩ ነው። ከየካቲት ጀምሮ አልፎ አልፎ ሲከሰት የነበረው “በህወሓት ታጣቂዎች” እና “በአካባቢው ሚሊሺያዎች” መካከል ሲደረግ የነበረው የተኩስ ልውውጥ ከሚያዝያ 5/2016 ዓ.ም. ጀምሮ ከፍ ባለ ሁኔታ ተካሂዶ ከሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወዲህ የነበረውን መዋቅር ቀይሮታል።
ከ20 በላይ ኢትዮጵያውያን የሞቱበት የጀልባ አደጋ የመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በስደተኛው አንደበት
ሰኞ ሚያዝያ 14/2016 ዓ.ም. የመን ውስጥ በስደት ሲንከራተቱ ቆይተው ወደ አገራቸው ለመመለስ የተነሱ ሰባ ሰባት ኢትዮጵያውያንን አሳፍራ ወደ ጂቡቲ ያቀናችው ጀልባ ወደ ባሕር ዳርቻው ብትቃረብም በሰላም ካሰበችበት አልደረሰችም። በገጠማት የመገልበጥ አደጋ ከ20 በላይ ኢትዮጵያውያን ባሕር ላይ ቀርተዋል። ከአደጋው የተረፈ አንድ ኢትዮጵያዊ አደጋው እንዴት እንደተከሰተ ለቢቢሲ ተናግሯል።
በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ እንዳሳሰባቸው የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር ገለጹ
በአማራ እና በትግራይ ክልሎች መካከል የይገባኛል ውዝግብ ባለባቸው አካባቢዎች ላይ እየታየ ያለው ሁኔታ በእጅጉ እንዳሳሰባቸው የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሐማት ገለጹ። ሊቀመንበሩ ባወጡት መግለጫ በሰሜን ኢትዮጵያ ራያ አላማጣ፣ ዛታ እና ኦፍላን ጨምሮ አወዛጋቢ በሆኑት አካባቢዎች ባሉ ማኅበረሰቦች መካከል “እየተባባሰ ያለውን ውጥረት” ስጋት ውስጥ ሆነው እየተከታተሉት መሆናቸውን አመልክተዋል።
በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ቦይንግ በወንጀል እንዲከሰስ ጠየቁ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን ከአምስት ዓመት በፊት ሕይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ለአደጋው መንስዔ የሆነው የአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ላይ የወንጀል ክስ እንዲመሠረት የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤትን ጠየቁ።
የደቡብ አፍሪካውያን የ30 ዓመታት የነጻነት ጉዞ እና ኤኤንሲ የሚፈተንበት ቀጣዩ አጓጊ ምርጫ
ከአፓርታይድ ሥርዓት መውደቅ በኋላ የብዙኃን መንግሥት ያቋቋመችው ደቡብ አፍሪካ ምርጫ ልታካሂድ ተቃርባለች። ላለፉት 30 ዓመታት አደሪቱን በበላይነት የመራው ኤኤንሲ ከባድ ፈተና ይገጥመዋል ተብሎ ይጠበቃል። ለመሆኑ ያለፉት የነጻነት ዓመታት እንዴት አለፉ? በዜጎቿ ሕይወት ላይስ ምን ለውጥ መጣ?
ምዕራባውያን ቢሊዮኖችን እያፈሰሱ ዩክሬንን የሚያስታጥቋት ዘመናዊ የጦር መሣሪያዎች
አሜሪካ ዩክሬንን የጦር መሣሪያ ለማስታጠቅ ከ60 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገንዘብ በዚህ ሳምንት አጽድቃለች። በሩሲያ የተከፈተባትን ወረራ ተከትሎ ጦርነት ውስጥ ለምትገኘው ዘመናዊ መሣሪያዎችን ለማቅረብ ምዕራባውያን ቢሊዮን ዶላሮችን እያፈሰሱ ነው። ለዩክሬን ምን ዓይነት የጦር መሣሪያዎች ናቸው የሚቀርቡት?
በትናንሽ ጀልባዎች ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ምን ያህል ስደተኞች ይገባሉ? ከየትኞቹ አገራት የመጡ ናቸው?
ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) በትናንሽ ጀልባዎች አቋርጠው ወደ ግዛቷ የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር መጨመር በእጅጉ ስላሳሰባት አዲስ ሕግ አዘጋጅታ ከአገሯ በማስወጣት ወደ ሩዋንዳ ለመውሰድ አቅዳለች። ከፈረንሳይ ተነስተው ባሕር በማቋረጥ ወደ ዩኬ ምን ያህል ስደተኞች ይገባሉ? የየትስ አገራት ዜጎች ናቸው?
ቻይና ‘ቀይ መስመር’ ያለችውን እንዳታልፍ አሜሪካን አስጠነቀቀች
የቻይን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሽንግተን የአገራቸውን “ቀይ መስመር” እንዳታልፍ ለአሜሪካው አቻቸው አስጠነቀቁ።
ቀሲስ በላይ መኮንን፤ በሐሰተኛ ሰነድ ገንዘብ ለማውጣት በተሞከረበት ቦታ የተገኙት “ሰዎች አታለዋቸው” መሆኑን ተናገሩ
ሐሰተኛ ሰነድ በመጠቀም ከስድስት ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማውጣት በመሞከር የተጠረጠሩት ቀሲስ በላይ መኮንን፤ ድርጊቱ በተፈጸመበት ቦታ የተገኙት “ሰዎች አታልለዋቸው” እንደሆነ ለፍርድ ቤት መግለጻቸውን ጠበቃቸው አቶ ቱሊ ባይሳ ለቢቢሲ ተናገሩ።
ከየፈርጁ
የአፍሪካ ኅብረት በሕገ ወጥ መንገድ ከንግድ ባንክ አካውንቱ ሊወጣ የነበረው ስድስት ሚሊዮን ዶላር አለመሳካቱን ገለጸ
የአፍሪካ ኅብረት ሚያዝያ 23 ቀን 2016 ዓ. ም. ባወጣው መግለጫ፣ በአዲስ አበባ ከተማ የአፍሪካ ኅብረት ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ስድስት ሚሊዮን ዶላር በሕገ ወጥ መንገድ ለማውጣት የተደረገው ሙከራ ሳይሳካ መቅረቱን ገልጿል።
በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉት ፖለቲከኛው በቴ ኡርጌሳ ሲታወሱ
በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ውስጥ ‘የማይናወጥ ጽናት’፣ ‘በሀሳብ ውይይት ጀርባውን የማይሰጥ’፣ እና ‘የግንባሩ አዲስ ትውልድ ምልክት’ እየተባሉ የተወደሱት አቶ በቴ ኡርጌሳ ሚያዝያ 3/2016 ዓ.ም. በመቂ ከተማ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለው ተገኝተዋል።
የብልፅግና ፓርቲ ‘የሚዲያ ሠራዊት’ አባላት በሐሰተኛ መረጃ ሥርጭት እና አሳሳች የፌስቡክ ዘመቻዎች ላይ መሳተፋቸውን የቢቢሲ ምርመራ አረጋገጠ
በገዢው ብልፅግና ፓርቲ በተለይም በአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ስር የሚንቀሳቀሱ እና ‘የሚዲያ ሠራዊት’ የሚል መጠሪያ ያላቸው የፓርቲው አባላት፤ መንግሥትን በሚተቹ እና በሚቃወሙ ግለሰቦች ላይ በፌስቡክ በተደረጉ የሐሰተኛ መረጃ እና በተቀናጁ ዘመቻዎች ላይ እንደተሳተፉ ቢቢሲ ያደረገው ምርመራ አረጋገጠ።
ዩክሬን እና ሩሲያ ሱዳን ውስጥ በእጅ አዙር ጦርነት እያካሄዱ ነው?
መስከረም 2016 ዓ.ም. ላይ በማይገመት ቦታ፣ ጨርሶ ሊገመቱ በማይችሉ ሁለት መሪዎች መካከል ስብሰባ ተደረገ። የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቭሎድሚር ዜሌንስኪ ከሱዳኑ መሪ ጄኔራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን ጋር በአየርላንድ በሚገኝ አየር ማረፊያ መገናኘታቸው ብዙዎችን አስደንቆ ነበር።
የውጭ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ከወጪ እስከ ችርቻሮ ንግድ ዘርፍ መግባታቸው በረከት ወይስ ስጋት?
ኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ለውጭ ባለሃብቶች ዝግ ሆነው የኖሩ የምጣኔ ሃበት ዘርፎችን እየከፈተች ነው። በቅርቡ ድግሞ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ተጠብቀው የነበሩት የወጪ፣ የገቢ፣ የጅምላ እና የችርቻሮ ንግድ ዘርፎች ክፍት እንዲሆኑ ተወስኗል። ይህ ውሳኔ የአገር ውስጥ ባላሃብቶችን እና ነጋዴዎችን ከገበያ ያስወጣል የሚሉ እንዳሉ ሁሉ፤ ውድድርን በመፍጠር ለሸማቾች አማራጮችን ያቀርባል የሚሉ አሉ። የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ምን ይላሉ?
የኢትዮጵያውያን ስደተኞች መዳረሻ የሆነችው ደቡብ አፍሪካ ያቀደችው የኢሚግሬሽን ማሻሻያ ምን ይዟል?
የበርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መዳረሻ የሆነቸው ደቡብ አፍሪካ እየሠራችበት ያለውን ‘የቅኝ ግዛት’ የኢሚግሬሽን ሥርዓት ልታሻሽል መሆኑን አስታውቃለች። የደቡብ አፍሪካ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር የአገሪቱ የኢሚግሬሽን ሕግጋት ጠበቅ ያሉ እንዲሆኑ እና የዜግነት እንዲሁም የጥገኝነት ሂደቶችን የሚያሻሽለውን አዲሱን ዕቅድ ይፋ አድርገዋል።
ኢራቃዊቷ የቲክቶክ ኮከብ ኦም ፋሃድ ባግዳድ ውስጥ በተተኮሰባት ጥይት ተገደለች
ኢራቃዊቷ የማኅበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪ ኦም ፋሃድ በባግዳድ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ውጭ በተተኮሰባት ጥይት ተገደለች።
ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ የተሳተፉበት የነፍስ አድን ጥረት በአሜሪካ
አሜሪካ ውስጥ በድንገት በደረሰ አደጋ ምክንያት ከመንገድ ወጥቶ በእሳት በተያያዘ መኪና ውስጥ የነበረ ግለሰብን ሕይወት ያተረፉ ሁለት ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ሌሎችም አድናቆት እየተቸራቸው ነው። መኪና ላይ በተገጠመ ካሜራ የተቀረጸው ቪዲዮ እንደሚያሳየው ትውልደ ኢትዮጵያዊያኑ እና ሌሎችም በመንገዱ ላይ ሲያልፉ የነበሩ ሰዎች በእሳት ከተያያዘው መኪና አንድን ግለሰብ ለመታደርግ ያደረጉትን አስደናቂ ጥረት አሳይቷል።
በአዲስ አበባ የግንባታ ድንጋይ እና አፈር ተደርምሶ የ4 ዓመት ህጻንን ጨምሮ የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ
በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ስሙ ጠሮ መስጂድ በተባለ አካባቢ ለቤት ግንባታ የተከመረ ድንጋይ እና አፈር ተንዶ የሰባት ሠዎች ሕይወት አለፈ።
እስራኤል እና ኢራን ጦርነት ውስጥ ቢገቡ ምን ይከሰታል? በወታደራዊ አቅምስ ይመጣጠናሉ?
ኢራን እና እስራኤል እስካለፈው ሳምንት ድረስ በእጅ አዙር እንጂ በቀጥታ ግጭት ውስጥ ገብተው አየውቁም። አሁን ግን በሚሳኤል እና በድሮኖች አንደኛው በሌላኛው ላይ ግልጽ ጥቃት መፈጸም ጀምረዋል። ለመሆኑ እስራኤል እና ኢራን ጦርነት ውስጥ ቢገቡ ምን ሊከሰት ይችላል? ሁለቱ አገራትስ በወታደራዊ አቅም ምን ያህል ይመጣጠናሉ?
ኢትዮጵያ፡ 56 በመቶ የሚሆኑ የሁለተኛ እና ሦስተኛ ክፍል ተማሪዎች ፊደል መለየት እንደማይችሉ ጥናት አመለከተ
በኢትዮጵያ ከሚገኙ የሁለተኛ እና ሶስተኛ ክፍል ተማሪች 56 በመቶዎቹ ምንም ዓይነት ቃል ማንበብ እንደማይችሉ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ባደረገው ጥናት አመልክቷል። አገልግሎቱ በጥናቱ ተሳተፊ ካደረጋቸው የሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል ቢያንስ አንድ ቃል ማንበብ የሚችሉ 37 በመቶ የሚሆኑት ብቻ እንደሆኑ በአገልግሎቱ የትምህርት ምዘናና ምርምር መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤፋ ጉርሙ (ዶ/ር) ለቢቢሲ ገልጸዋል። የተቀሩት 63 በመቶዎቹ አንድም ቃል ማንብብ የማይችሉ (Zero renderers) ናቸው።
አጃኢብ!
በመስቀል ላይ የሚፈጸም ስቅላት እንዴት እና የት ተጀመረ?
በክርስትና እምነት ተከታዮች ከትንሳኤ ዕለት የምትቀድመዋን ዕለተ አርብ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት ቀን በማለት በየዓመቱ ያስቧታል። ይህች ዕለትም ከብዙ እንግልት እና ስቃይ በኋላ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰው ልጅ ከተዘፈቀበት ሃጥያት ለማንጻት ሲል በመስቀል ላይ የከፈለው የመስዋዕትነት የሚዘከርባት ናት። የእምነቱ ተከታዮችም ዕለቱን ኢየሱስ ለሰው ልጆች ፍቅር ሲል ራሱን አሳልፎ የሰጠበት ነው ብለው ያምናሉ።
የቢቢሲ ጋዜጠኛ አሳዛኝ የጋዛ ገጠመኞች
ከጋዛ ለቢቢሲ የሚዘግበው ጋዜጠኛና አስደንጋጭ ገጠመኞቹ
ደሞዝ በጊዜው የማይከፈላቸው የመንግሥት ሠራተኞች ጭንቀት በወላይታ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ውስጥ ያሉ የመንግሥት ሠራተኞች ደሞዛቸው ይዘገያል ወይም ተቆራርጦ ነው የሚከፈላቸው። በዚህም ሳቢያ ሠራተኞች ሥራቸውን በአግባቡ ማከናወን ባለመቻላቸው ሕብረተሰቡም አገልግሎት እያጣ መሆኑን እራሳቸው ሠራተኞቹ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ዱባይን ያጥለቀለቃት ጎርፍ ደመናን ወደ ዝናብ በሚቀይረው ቴክኖሎጂ የተፈጠረ ይሆን?
ዱባይ ከሰሞኑ አውሎ ንፋስ በቀላቀለ ከባድ ዝናብ መመታቷን ተከትሎ በጎርፍ ተጥለቅልቃ ነበር። በ75 ዓመት ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ የተባለው ዝናብ ከፍተኛ ንብረት አውድሟል፣ እንቅስቃሴ ቀጥ እንዲል አድርጓል፣ እንዲሁም ሕይወት ቀጥፏል። ከዚህ ዝናብ ጋር ተያይዞም ደመናን ወደ ዝናብ ስለሚቀይረው ቴክኖሎጂ በርካታ መላምቶች እየተሰነዘሩ ነበር።
ስለ ክትባት ያልተረጋገጡ የሴራ ትንተናዎችን የሚያሠራጩት ተጽእኖ ፈጣሪ ፓስተር
“ክራይስት ኤምባሲ” የተባለው ቤተክርስቲያን መሥራች እና መሪ የሆኑት ናይጄሪያዊው ፓስተር ክሪስ ኦያኪሂሎሜ በስብከታቸው ውስጥ የሚያስተላልፉት መልዕክት ላይ ክስ ይቀርብባቸዋል። በተለይ በክትባት ዙሪያ የሚያሠራጩት የሴራ ትንተና በተለያዩ የአፍሪካ አገራት የሚገኙ ተከታዮቻቸውን ጤና አደጋ ላይ የሚጥል ነው እየተባለ ነው። ፓስተሩ ምን አሉ?
በእስራኤል ጥቃት ከተገደለች እናት ማህጸን በሕይወት ወጥታ የነበረችው ጨቅላ አረፈች
እስራኤል በደቡባዊ ጋዛ በፈጸመችው ጥቃት ከተገደለች ፍልስጤማዊት እናት ማህጸን በሕይወት መውጣት ችላ የነበረችው ጨቅላ ከቀናት በኋላ አረፈች።
ቪዲዮ, ምንጩ ከኢትዮጵያ የሆነው ቡና ለጤና እና ለዓለም ሥልጣኔ ስላበረከተው አስተዋጽኦ በጥቂቱርዝመት, 6,19
በዓለም ላይ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በየዕለቱ ቡና ይጠጣሉ። ቡና ቢያንስ ላለፉት 1500 ዓመታት እንደተጠጣ ይነገራል። ምንጩ ከኢትዮጵያ የሆነው ይህ ፍሬ ዛሬ ዓለም ላለችበት ዕድገትም የራሱን አስተዋጽኦ አድርጓል በማለት ምሁራን ይጠቅሱታል። በሌላ በኩል በሰውነታችን ውስጥ የተለያዩ በሽታዎችን በመከላከልና አዕምሮን በማንቃት አስተዋጽኦ እንዳለው የጤና ሙያተኞች ይመሰክራሉ። ቢቢሲ በዚህ ቪዲዮ ስለቡና ታሪካዊ ዳራ፣ ጠቀሜታዎች እና የጎንዮሽ ጉዳቶች በአጭሩ አቅርቧል።
በዓለም ላይ ግዙፍ ገደሎች የመኖርያ መንደሮችን እየዋጡ ነው
የአየር ንብረት ለውጥ ለሸለቆዎች መሸርሸር ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ከፍተኛ የዝናብ መጠን እንዲኖር በማድረግ አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል።
የኢራን መንግሥትን የተቃወመው ራፐር ሞት እንደተፈረደበት ጠበቃው ተናገረ
መንግሥትን የሚቃወሙ እንቅስቃሴዎችን በመደገፍ የታሰረው ኢራናዊ ራፐር በሞት እንዲቀጣ በፍርድ ቤት ውሳኔ መተላለፉን ጠበቃው ገለጸ።
ታዋቂው ደራሲ ሳልማን ሩሽዲ በስለት ተወግተው ዐይናቸውን ያጡባትን ዕለት ሲያስታውሱ
ታዋቂው ደራሲ ሰር ሳልማን ሩሽዲ ከሦስት አስርት ዓመታት በፊት ባሳተሙት መጽሐፋቸው ምክንያት ተደጋጋሚ የግድያ ዛቻ ሲሰነዘርባቸው ቆይተው ከሁለት ዓመት በፊት ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል። በዚህም አንድ ዐይናቸውን ያጡ ሲሆን፣ ያቺን ዕለት ሲያስታውሱ የዐይን ብርሃናቸውን ማጣታቸው ማጣታቸው በእጅጉ እንደሚያንገበግባቸው ይናገራሉ።
በቦኮሃራም የታገተችው ናይጄሪያዊት ተማሪ ከ10 ዓመት በኋላ ሦስት ልጆችን ወልዳ ነጻ ወጣች
ከአስር ዓመት በፊት በቦኮሃራም ታጣቂዎች ታግተው ከነበሩ ሴቶች መካከል አንዷ የሦስት ልጆች እናት ሆና በናይጄሪያ መንግሥት ወታደሮች ነጻ ወጣች።
አደገኛ በመሆኑ ከገበያ እንዲሰበሰብ ስለተባለው የህጻናት የሳል ሽሮፕ ምን እናውቃለን?
ቢያንስ አምስት የሚሆኑ የአፍሪካ አገራት የተወሰኑ የጆንሰን ኤንድ ጀንሰን የሳል ሽሮፖች ከገበያ እንዲሰበሰቡ አዘዋል። “እጅግ ከፍተኛ” መርዛማ እና የመግደል አቅም ያለው ዳይትሊን ግላይኮል የተባለውን ንጥረ ነገር በምርመራ እንዳገኙበት ገልጸዋል።
የተመለሱ ጥያቄዎች
ፍልስጤማውያን በእስራኤል ላይ ሲያካሂዱት የቆየው ‘ኢንቲፋዳ’ ምንድን ነው?
በቅርቡ በአሜሪካ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እየተካሄዱ ካሉ የጋዛን ጦርነት ከሚቃወሙ ሰልፎች ጋር ተያይዞ ‘ኢንቲፋድ’ የሚለው ቃል በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል። ቃሉ ብዙ ጊዜ የሚያያዘው ፍልስጤማውያን በእስራኤል ላይ ከሚያስነሱት መረር ካለ ተቃውሞ ጋር ነው።
ቪዲዮ, በበርካታ አገራት ከተሞችን በማውደም አሳሳቢ አደጋን እየጋረጠ ያለው የመሬት መንሸራተትርዝመት, 3,44
በዚህ ዘመን የመሬት መንሸራተት በበርካታ የዓለም አካባቢዎች አሳሳቢ እየሆነ የመጣ ክስተት ነው። ባለሙያዎች እንደሚሉት ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል። በደቡብ አሜሪካ እና በአፍሪካ የሚገኙ አንዳንድ ከተሞችም ለውድመት ሲዳረጉ፣ በርካታ ሰዎችም ሕይወታቸውን አጥተዋል። የመሬት መሸርሸር ተፈጥሯዊ ቢሆንም ሰው ሰራሽ ምክንያቶች እንዳባባሱት ባለሙያዎች ይገልጻሉ። በዚህም ሳቢያ በአፍሪካ እና በደቡብ አሜሪካ ያሉ ከተሞች አደጋ ተጋርጦባቸዋል።
በመላው ዓለም የሚከበረው የምድር ቀን ምንድን ነው? ምንስ ዓላማ አለው?
የምድር ቀን በመላው ዓለም ሚያዝያ 14/2016 ዓ.ም. (በአውሮፓውያኑ ሚያዝያ 22) በተለያዩ ዝግጅቶች በመላው ዓለም ይታሰባል። ይህ የምድር ቀን ምንድን ነው? ምንስ ዓላማ አለው?
በተለያየ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ልጆቻችንን ስለ አደጋዎች እንዴት ማስተማር እንችላለን?
ዕድሜ ሲጨምር ስለ አደጋ ያለ ግንዛቤም ያድጋል። ልጆች ግን ሊገጥማቸው የሚችለውን አደጋ ባለማወቅ በቀላሉ ለጉዳት ሊዳረጉ ይችላሉ። ታዲያ ልጆችን ስለ አደጋ እና ቅድመ ጥንቃቄ ማስተማር የሚቻለው እንዴት ነው? በተለያየ ዕድሜ ላይ ያሉ ልጆችን ስለ አደጋ ማስተማር የሚቻልባቸው መንገዶች አሉ።
ቡና እንዴት በዓለማችን በብዙዎች የሚወደድ አነቃቂ ፍሬ ሊሆን ቻለ?
እንቅልፍ ከማትተኛው የኒው ዮርክ ከተማ እስከ ኢትዮጵያ ተራሮች ድረስ ዝናው የናኘ ነው፤ ቡና። ሚሊዮኖች ሳይጎነጩት መዋል አይቻላቸውም። ቡና ለ15 ክፍለ ዘመናት የሰው ልጆች ባህል ማዕከል ሆኖ ኖሯል። አንዳንዶች የ17ኛው እና የ18ኛው ክፍለ ዘመን አብርሆት ከቡና ነው የመነጨው ይላሉ።
የኢድ አል-ፈጥር በዓል ቀን የሚወሰነው እንዴት ነው?
1445ኛው የኢድ-አልፈጥር በዓል ዛሬ ረቡዕ ሚያዚያ 2/2016 በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ቅዱስ የሆነው የረመዳው ወር ሲጠናቀቅ ከፍ ያለ ሃይማኖታዊ ትርጉም የሚሰጠው የኢድ-አልፈጥር በዓል ይከበራል።
የአእምሮ ጤና እክል የሆነው ባይፖላር ዲስኦርደር ምንድን ነው? ለምንስ ከታዋቂው ሠዓሊ ጋር ተያያዘ?
በተቃራኒ የስሜት ጽንፎች ውስጥ መዋለል (ባይፖላር ዲስኦርደር) ከ100 ሰዎች ውስጥ በአንድ ሰው ላይ ይከሰታል። ስለዚህ የአእምሮ ጤና እክል ግንዛቤን ለማስፋት መጋቢት 21 በየዓመቱ የባይፖላር ዲስኦርደር ቀን ይታሰባል። ይህ ቀን ደግሞ የታዋቂው ሠዓሊ ቪንሰንት ቫን ጎ የልደት ቀን ነው። ዕለቱ ለምን ከእሱ ጋር ተያያዘ? ቫን ጎ ባይፖላር የአእምሮ ጤና ችግር ነበረበት?
የአሜሪካን ገመና ለዓለም ይፋ ያደረገው ጁሊያን አሳንጅ ማን ነው?
የአሜሪካን ገመና ለዓለም ይፋ ያደረገው ዊክሊክስ የተሰኘው ድረ ገጽ መሥራች ጁሊያን አሳንጅ ከሰሞኑ የበርካታ መገናኛ ብዙኃን ዋነኛ ርዕሰ ጉዳይ ሆኗል።
ችላ ተብለው በአሳሳቢ ደረጃ በመላው ዓለም እየተስፋፉ የመጡት የአባላዘር በሽታዎች
እንደ የዓለም የጤና ድርጅት መረጃ በመላው ዓለም በየቀኑ ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች በግብረ ሥጋ ግንኙነት በሚተላለፉ በሽታዎች ይያዛሉ። ነገር ግን በትክክል በወሲብ የሚተላለፍ በሽታ ምንድን ነው? ዓይነቶቹ እና ምልክቶቹስ ምንድን ናቸው? ራሳችንን እንዴት መጠበቅ እንችላለን?
ማንኮራፋት እንዴት ትዳርን እስከ ማፍረስ ሊያደርስ ይችላል? ምንስ መፍትሄ አለው?
የማንኮራፍት መዘዙ እንቅልፍ ማሳጣት ብቻ አይደለም። ለሚያንኮራፋው እና ከጎን ለሚተኛ አካላዊ እና የአእምሮ ጤና ጉዳት ያስከትላል። ትዳር ሊያፈርስ ይችላል።
ፆም በሰውነታችን ውስጥ የሚያስከትለው ለውጥ እና የሚሰጠው ጥቅም ምንድን ነው?
ለእስልምና እና ለክርስትና እመነት ተከታዮች ዋነኞቹ የፆም ወቅት የሆኑት ረመዳን እና ዓቢይ ፆሞች ተጀምረዋል። የሁለቱም እምነቶነቶች ምዕመናን የፆሙን ጊዜ በየራሳቸው ሥርዓት እና ደንብ መሠረት የሚከውኑት ሲሆን፣ በየዕለቱ ለረጅም ሰዓታት ከምግብ እና ከውሃ ርቀው ይቆያሉ። በዚህ ጊዜ ታዲያ ፆም በሰውነት ላይ ምን ለውጥን ያስከትላል? ምንስ ጥቅም አለው?
በረመዳን የፆም ወቅት የትኞቹን ዓይነት ምግቦች መመገብ፣ የትኞቹንስ መተው አለብን?
ረመዳን የፆም ወቅት ሙስሊሞች በጉጉት የሚጠብቁት ጊዜ ነው። ከማለዳ ጀምሮ አስከ ምሽት ድረስ ምግብ ሳይቀመስ የሚቆይበት የፆም ጊዜ የመጀመሪያ ቀናት ለአንዳንዶች ፈታኝ ነው። በፆሙ ወቅት መደበኛ እንቅስቃሴያችንን እያደረግን ያለድካም ለመቆየት የሚያስችሉ ዘዴዎችን የሥነ ምግብ ባለሙያዎች ይመክራሉ። በዚህ ወቅት ምን ዓይነት ምግቦችን መመገብ፤ የትኞችንስ ማስቀረት አለብን?